ዳሎል፤ ዝናብ የማይዘንብበት ቦታ
በኢትዮጵያ አፋር ክልል የሚገኘው ዳሎል፤ አረንጓዴ የአሲድ ኩሬዎች፣ መርዛማ ክሎሪን እና ሰልፈሪክ ጋዞች ያሉት ብዙም ካልተለመዱት የሃይድሮተርማል አካባቢዎች አንዱ ነው። ይህ አካባቢ ብዙ ቱሪስቶችን እየሳበ ይገኛል።
የእግር ጉዞ በሞቃትማው ዳሎል
በኢትዮጵያ አፋር ክልል የሚገኘው የጨው ገደል ቦታውን የአፖካሊፕስ ፊልም የቀጥታ ትዕይንት እንዲመስል አድርጎታል። የደንከል ዝቅተኛ ቦታ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ድንበር ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በምድር ላይ ካሉት በጣም ሞቃታማ እና ተስማሚ ካልሆኑ ቦታዎች አንዱ ነው። የሙቀት መጠኑ 50 ዲግሪ ሴልሺየስ ወይም 122 ዲግሪ ፋራናይት የተመዘገበ ሲሆን፤ እዚህ ቦታ ፈጽሞ ዝናብ አይዘንብም።
የዳሎል የሃይድሮተርማል ስርዓት
ቱሪስቶች የዳሎል ሰልፈር ምንጭን ይጎበኛሉ። በዓለም ላይ ካሉት በጣም ያልተለመዱ የሃይድሮተርማል አካባቢዎች አንዱ። በኪሎ ሜትሮች የሚረዝመውን የጨው ሐይቅ በጂፕ መኪና ይሻገራሉ። የአካባቢው ነዋሪዎች ግን በግመል መጓዝን ይመርጣሉ። ዳሎል የሚለው ቃል በአፋር ህዝብ የተሰጠ ሲሆን ትርጉሙ የተበታተነ ማለት ነው።
የላብ ዋጋ
የደንከል ዝቅተኛ ቦታ ከፍተኛ መጠን የጨው ወይም የ«ነጭ ወርቅ» ክምችት አለው። ይህም ለአርብቶ አደሩ የአፋር ህዝብ የህልውና መሰረት ነው። ጉልበት የሚጠይቀውን የጨው ጋንፉር (አሞሌ ጨው) መሬት ላይ ለመጥረብ መሳሪያቸውን ይዘው በጠዋት ወደ ሞቃታማው ቦታው ያመራሉ። ይህንን ጨው በአካባቢው ገበያ ለሽያጭ ያቀርቡታል። .
መርዛማው ማዕድን
ዳሎል እየተባለ የሚጠራው በ1926 የዶሎል እሳተ ጎመራ ከፈነዳ በኋላ የተፈጠረ አስገራሚ ክስተት ነው። ወደ 30 ሜትር ወይም ከጨው በረሃው 100 ጫማ ርቀት ላይ ይነሳል። ከብዙ የአካባቢው ፍልውሃዎች ጋር የተዛመደ እና የሰልፈር ሐይቅን የሚሞላ የመሬት መንቀጥቀጥ እንቅስቃሴ አሁንም ድረስ አለ። ሁሉም ቦታ ላይ የገማ እንቁላል የሚመስል ሽታ አለ።
የተለዬ አፈጣጠር
ሰልፈሩ ያለበት ለመድረስ ፍል ውሃው በድንጋዩ የተለያዩ ንጣፍች ውስጥ ሰርስሮ መግባት አለበት። በዚህ ሂደት ውስጥ ሰልፈርን፣ ብረትን እና ጨውን ነጻ ያደርጋል። እነዚህ ንጥረ ነገሮች በቢጫ ቀይ እና ነጭ ሽፋን የተለዬ ቅርጾችን ይፈጥራሉ። አስደናቂ የቀለሞች ትዕይንት።
ሕይወት ያለው ነገር ፈፅሞ ሊኖር አይችልም
በጎርጎሪያኑ በጥቅምት 2019 ዓ/ም ሳይንቲስቶች በተፈጥሮ፣ ሥነ-ምህዳር እና በዝግመተ ለውጥ መፅሄት ላይ ባሳተሙት አንድ ዘገባ ፤በዳሎል የጨው ኩሬ ውስጥ ሕይወት የለም። እጅግ በጣም ዝቅተኛ የሆነውን የፒኤች መጠን የመከላከል አቅም ስለሌላቸው፤ የሚቋቋም የሚችሉት ረቂቅ ተሕዋስያን እንኳን እዚያ ለመኖር ምንም ዕድል የላቸውም። ቦታው ከ 35 በመቶ በላይ የሆነ የጨው ይዘት እና ከ108 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ሙቀት አለው።
ብርቅዬ እሳተ ገሞራ
የኤርታሌ እሳተ ገሞራ በደንክል ዝቅተኛ ቦታ ውስጥም ይገኛል። ይህ ልዩ እሳተ ገሞራ በዓለም ዙሪያ በራሳቸው ጉድጓድ ውስጥ የቀለጠ የአለት ሐይቅ ካላቸው ስድስት እሳተ ገሞራዎች ውስጥ አንዱ ነው። በ613 ሜትሮች ከፍታ ወይም በ2011 ጫማ ከፍታ ላይ ያለውን የእሳተ ገሞራ ግንብ ደፋር ጎብኝዎች በራሳቸው ሀላፊነት ለማየት ይችላሉ።
የእረፍት ጊዜን በሀሩር
በበጋ ወቅት የአየር ንብረት ሙቀትን እየፈለጉ ከሆነ ፣ በአማካኝ 35.6 ዲግሪ ሴልሺየስ የሙቀት መጠን ያለው ጥሩ መድረሻ ቦታ ነው። በፕላኔቷ ላይ በጣም ሞቃታማው ቦታ ነው። የዚህ ክልል ትልልቅ ክፍሎች ከባሕር ጠለል በታች 125 ሜትር ነው።